የቀሪ ሁለት ወራት ዕቅዶችን ለማሳካት የሚያድሩ...

image description
- ክስተቶች News    0

የቀሪ ሁለት ወራት ዕቅዶችን ለማሳካት የሚያድሩ ስራዎች እንዳይኖሩ በጊዜና በጥራት የተደገፈ አግልግሎት መስጠት እንደሚገባ ተገለፀ ።

የቀሪ ሁለት ወራት ዕቅዶችን ለማሳካት የሚያድሩ ስራዎች እንዳይኖሩ በጊዜና በጥራት የተደገፈ አግልግሎት መስጠት እንደሚገባ ተገለፀ ። 

ይህ የተገለፀው በቀሪ ሁለት ወራት ማፍጠኛ እቅድ ላይ በየዘርፉ ከባለሙዎች ጋር በተደረገ ውይይት ላይ ነው። 

የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ ጠቅላላ ካውንስል በበጀት ዓመቱ 10 ወራት ዕቅድ አፈጻፀም ላይ በመምከር በቀሪ ሁለት ወራት ማፍጠኛ ዕቅድ ላይ ውይይት በማድርግ አቅጣጫ ማስቀመጡ ይታወሳል።

በዚህ መነሻነት በቀሪ ሁለት ወራት ይከናወናሉ ተብለው በተለዩ ዋና ዋና የትኩረት መስኮች ዙሪያ በየዘርፉ ከባሙያዎች ጋር ውይይት ተደርጓል ፡፡

በውይይቱ የገቢ አቅምን ማሳደግ፣ የአገልግሎት አሰጣጥ ጥራት፣ የባለሙያዎች አቅምና ሰነ ምግባር ትኩረት ተደርጎባቸዋል፡፡

የገቢ አቅማችንን ለማሳደግ ስናስብ
የአገልግሎት አሰጣጣችንን ፈጣንና ጊዜ ቆጣቢ ማድረግ ቁልፍ ተግባራችን ሊሆን ይግባል ተብሏል ፡፡    

ለዚህም የሚያድሩ ስራዎች እንዳይኖሩ በቅንነትና በትብብር መስራት እንደሚገባም ተመላክቷል ።

በአገልግሎት አሰጣጥ ወቅት የሚታዩ
የስነ ምግባር ጉድለቶች የሪፎርም ስራዎቻችን ማነቆዎች በመሆናቸው ተገቢው ክትትል ተደርጎ የእርምት እርምጃ ይወሰዳልም ተብሏል ፡፡


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.