
የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ 5ኛ ዙር የመሬት ሊዝ ጨረታ አሸናፊዎችን ውል ማዋዋል ጀመረ፡፡
የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ 5ኛ ዙር የመሬት ሊዝ ጨረታ አሸናፊዎችን ውል ማዋዋል ጀመረ፡፡
ሚያዝያ 24/2017 (መልአ)
የአዲስ አበባ መሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ የ5ኛ ዙር የመሬት ሊዝ ጨረታ አሸናፊዎችን ውል ማዋዋል መጀመሩን የጨረታ ኮሚቴ አስተባባሪ አቶ ሀብታሙ ተስፋዬ ገልፀዋል፡፡
በዚህ ጨረታ በዘጠኝ ክፍለ ከተሞች 427 ቦታዎች ለጨረታ ቀርበው የነበሩ ሲሆን ተገቢውን የጨረታ ሂደት ተከትሎ የ380 ቦታዎች አሸፊዎች ተለይተው ሚያዚያ 15/2017 ዓ/ም በታተመው አዲስ ልሳን ጋዜጣ ስም ዝርዝራቸው ይፋ መደረጉ ያታወቃል፡፡
በዚህም መሰረት ቢሮው የአሸፊናዎችን ስም ዝርዝር ይዞ የወጣው አዲስ ልሳን ጋዜጣ ገበያ ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ አስር የስራ ቀናት ለም ሆቴል አከባቢ በሚገኘው የተቋሙ ዋና መስሪያ ቤት ውል እያዋዋለ ነው፡፡ ሂደቱ ሐሙስ ሚያዚያ 30/2017 ዓ/ም የሚጠናቀቅ ሲሆን አሸናፊዎች በተገለፀው ቀነ ገደብ ውስጥ በአካል ቀርበው ውል የማይፈጽሙ ከሆነ በሊዝ ደንቡ መሰረት ሁለተኛ ለወጡ ተጫራጮች ጥሪ እንደሚደረግ ከጨረታ ኮሚቴ ያገኘነው መረጃ ያሳያል ፡፡
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.