ዝቅተኛ አፈፃፀም የታየባቸውን ተግባራት በመለየት...

image description
- ክስተቶች News    0

ዝቅተኛ አፈፃፀም የታየባቸውን ተግባራት በመለየት በትኩረት ልንሰራባቸው ይገባል ።አቶ መኮንን ያዒ

ይህ የተባለው ልምድ በሚቀመርበት በወርቃማው ሰኞ መረሃ ግብር ላይ ነው።
ሐምሌ 7/2017 /መልአ/
-------------------------------
ከማዕከል እስከ ክፍለ ከተማ የቢሮ አመራርና ሰራተኞች የተሳተፉበት የዛሬው የወርቃማ ሰኞ መረሃ ግብር ራስን ማጎልበ እንዴት ፣በምን እና   ለምን በሚሉ ጉዳዮች ላይ ትኩረት ያደረገ ነው።

የእለቱ ተጋባዥ እንግዳ ዶ/ር አደራ አብደላ በነዚህ ርዕሰ ጉዳች ላይ  በኦን ላይን ያቀረቡት ሰነድ እንደሚያመላክተው ራስን ማጎልበት አዲስ አስተሳሰብ ፣አዲስ ማንነት እና አዲስ እይታ እንዲኖረን ያስችላል ። 

ለዚህም ጤናችንን መጠበቅ ፣ ማንበብ ፣መንፈሳዊ ህይወታችንን ማጎልበት፣የፋይናንስ አቅማችንን ማሳደግ፣ የተግባር ሰው ስለመሆን ማቀድ፣ውሎአችንን ማስተካከል እና በቂ እረፍት መውሰድ ይኖርብናል ያሉት ዶ/ር አደራ ይህም በተሰማራንበት የስራ መስክ ውጤታማ እንድንሆን ያስችለናል ብለዋል።

በዋናነት ግን የውስጥ ተነሳሽነት ወሳኝ ስለመሆኑ በገለፃቸው ያብራሩት ደ/ር አደራ  ለዚህም በየዕለቱ  ራሳችንን በመገምገም የቱ ጋር ነው ያለሁት በማለት ራስን መጠየቅ ይገባል ብለዋል::

በየዕለቱ እራስን በማብቃትና በማጎልበት ንቁና ውጤታማ ሰው መሆን ይኖርብናል ያሉት ደግሞ የቢሮ ኃላፊ አቶ መኮንን ያዒ በተሰጠን የሥራ ዕቅድ ውጤታማ ያልንሆባቸውን ተግባራት ለይተን በትኩረት ልንሰራ ይገባናል ብለዋል ።

አሁን ላይ ያለፈውን ዓመት በሚገባ ገምግመን ለአዲሱ አመት እየተዘጋጀን ነው ያሉት ኃላፊው የተሻለ አፈፃፀም ያላቸውን ለይተና እውቅና በመስጠትም እናተጋለን በማለት ገልፀዋል። 

በየዕለቱ በሚካሄደው ወርቃማ ሰኞ በሚቀርቡ እንግዶች የሚነሱ ሃሳቦች ጥሩ ልምድ የምናገኝባቸው በመሆናቸው ተጠናክሮ ይቀጥላል ሲሉም ተናግረዋል።

ለበለጠ መረጃ የማህበራዊ ትስስር ገፆቻችንን Like, Follow, subscribe በማድረግ ያግኙ 
👇👇👇👇👇👇
Website: - https://www.aalb.gov.et
Face book:-Addis Ababa City Land Development Administration and Bureau
Email ፦addisabababacityland@gmail.com  
Telegram ፦https://t.me/Addis Land
Youtube.https://www.youtube.com/@AddisAbabaCityLandDevelopment 
Tiktok.https፦//www.tiktok.com/@aa.land.administrator?_t=ZM-8uSveGuoY8T&_r=1


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.