
የኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ከፍተኛ አፈጻጸም ላስመዘገቡ ወረዳዎችና ባለሙያዎች እውቅና ሰጠ።
የኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ከፍተኛ አፈጻጸም ላስመዘገቡ ወረዳዎችና ባለሙያዎች እውቅና ሰጠ።
ሐምሌ17/2017/መልአ
በመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ የኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በ2017 በጀት ዓመት አመርቂ አፈጻጸም ላስመዘገቡ ወረዳዎችና ሰራተኞች የእውቅና እና የምስጋና ፕሮግራም አዘጋጅቷል ።
መርሐ ግብሩ በበጀት ዓመቱ የላቀ አፈጻጸም ያስመዘገቡ ሰራተኞችን ለማመስገን እና ዝቅተኛ ውጤት ያመጡ ሰራተኞችን በማንቃት በተያዘው አዲሱ በጀት ዓመት ለተገልጋዮች የተሻለ አገልግሎት እንዲሰጡ ለማንቃት ታስቦ መዘጋጀቱን የቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ኃላፊ ወ/ሮ ሳምራዊት በቀለ ተናግረዋል ።
ተሸላሚ ሰራተኞች በበኩላቸው እውቅናው የፉክክር መንፈስን የሚፈጥርና ለቀጣይ ስራቸው የማስፈንጠሪያ አቅም ሆኖ እንደሚያገለግላቸው ለቢሮው ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት አስተያየታቸውን ሰንዝረዋል።
ለበለጠ መረጃ የማህበራዊ ትስስር ገፆቻችንን Like, Follow, subscribe በማድረግ ያግኙ
👇👇👇👇👇👇
Face book :-Addis Ababa City Land Development Administration and Bureau
Email ፦addisabababacityland@gmail.com
Telegram ፦https://t.me/AddisLand
Youtube፦https://www.youtube.com/@AddisAbabaCityLandDevelopment
Tiktok.https፦//www.tiktok.com/@aa.land.administrator?_t=ZM-8uSveGuoY8T&_r=1
Instagram፥https://www.instagram.com/addisababa
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.