6ኛው ዙር የመሬት ሊዝ ጨረታ ማስታወቂያ

image description
- ክስተቶች News    0

6ኛው ዙር የመሬት ሊዝ ጨረታ ማስታወቂያ

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ የከተማ ቦታን በሊዝ ለማስተላፍ በአዋጅ ቁጥር 721 /2004 በተሰጠው ስልጣን መሰረት በ6ኛው ዙር የመሬት ሊዚ ጨረታ በኮልፌ ቀራኒዮ፣ በየካ፣ በአቃቂ ቃሊቲ፣ በአዲስ ከተማ፣ በጉለሌ፣ በንፋስ ስልክ ላፍቶ፣ በለሚ ኩራ እና በአራዳ ክፍለ ከተሞች የሚገኙና ለተለያዩ አገልግሎቶች የተዘጋጁ ቦታዎችን በሊዝ ጨረታ አወዳድሮ ለማስተላለፍ ይፈልጋል።
ስለሆነም ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን 
የ telebirr M-PESA 
የ CBE birr 
የ Awash Bank, 
የ Coop Bank እና 
የ Sinqee Bank 
በመጠቀም በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ የሂሳብ ቁጥር 1000004337631 ከአካውንታችሁ ተቀናሽ በማድረግና በመክፈል የጨረታ ሰነዱን በዌብ ሳይት landleasedocument.aalb.gov.et (https://www.landleasedocument.aalb.gov.et) በኦንላይን መግዛት ይችላሉ።
ተጫራቾች ከላይ በተዘረዘሩት ክፍለ ከተሞች በሊዝ ጨረታ የቀረቡ ቦታዎችን አጠቃላይ ሁኔታ በሰፍራው ተገኝቶ በማየት ዋጋ ማቅረብ እንደሚችሉም ቢሮው ያስታውቃል።
ማሳሰቢያ ፡- አንድ ተጫራች በአንድ የጨረታ ዙር ከአንድ ቦታ በላይ መጫረት እንደማይችል ቢሮው እያሳሰበ ተጫርቶ ከተገኘ ተጫራቹ ከጨረታ ውጪ ይሆናል፡፡
የጨረታውን ዝርዝር መረጃ የአዲስ ልሳን ጋዜጣ የማክሰኞ ሐምሌ 22 ቀን 2017 ዓ/ም ልዩ ዕትም ይመልከቱ።


ለበለጠ መረጃ የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ
በስልክ ቁጥር + 251111570595 
Telegram፡-t.me/addisland
Fecebook፡-Addis Abeba City Land Development Administration and Bureau ይጎብኙ


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.