
6ኛው ዙር የመሬት ሊዝ ጨረታ መራዘም እና የተሰረዙ ቦታዎች
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ ለ6ኛዉ ዙር የመሬት ሊዝጨረታ በኮልፌ ቀራንዮ፣ በየካ፣ በአቃቂ ቃሊቲ፣ በአዲስ ከተማ፣ በጉለሌ፣ በንፋስ ስልክ ላፍቶ፣ በለሚ ኩራ እና አራዳ ክ/ከተሞች የሚገኙ ለተለያዩ አገልግሎቶች የተዘጋጁ ቦታዎችን በጨረታአወዳድሮ በሊዝ ለማስተላለፍ ሐምሌ 22/2017ዓም በአዲስ ልሳን ጋዜጣ በልዩ ዕትም በማሳተምከሐምሌ 22/2017ዓ.ም ጀምሮ እስከ ነሐሴ 05/2017ዓ.ም ድረስ የሚቆይ የጨረታ ሰነድ ሽያጭእያከናወነ መሆኑ ይታወቃል፡፡
ይሁን እንጅ የጨረታ ሰነድ ሽያጩን ማራዘም አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ ከነሐሴ06/2017ዓ.ም ጀምሮ እስከ ነሐሴ 12/2017ዓ.ም ከቀኑ 9፡00 ሰዓት ድረስ ለ5 ተከታታይ የስራቀናት የጨረታ ሰነድ ሽያጩ የተራዘመ መሆኑን እየገለጽን፡-
1. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ለማግኘት ከቴሌ ብር ከአካዉንታችሁ ተቀናሽ በማድረግና ክፍያ በመፈጸም የጨረታ ሰነዱን ወደ ዌብ ሳይት (https://www.lndleasedocument.aalb.gov.et/)https://www.lndleasedocument.aalb.gov.et (https://www.lndleasedocument.aalb.gov.et/)) በመግባት መግዛትና ሰነዱን ፕሪንትበማድረግ መወዳደር ይኖርባቸዋል፡፡
ቦታዎቹን በነዚሁ ቀናት በስራ ሰአት ጠዋት 3፡00 ሰአት እና ከሰአት 8፡00 ሰአት በየክ/ከተማዉ የመሬት ልማትና አስተዳደርቅ/ጽ/ቤት በመገኘት መጎብኘት የሚቻል መሆኑን እየገለጽን
ተጫራቾች
የጨረታ መልስ ማቅረቢያ ሰነድ
ሲፒኦ
የግንባታ አቅም ማሳያ ማስረጃ
ሰነዱን ለመግዛት በቴሌ ብር የከፈሉበትን ደረሰኝ እና
ሌሎች መያያዝ ያለባቸዉን በተጫራቾች መመሪያ ላይ የተገለጹትን በመጨመር የጨረታ ሰነዶችን በኤንቨሎፕ በማሸግ ነሐሴ 12/2017 ዓ.ም ከቀኑ 11፡30 ሰዓት ድረስ ለም ሆቴል አከባቢ ኤም ኤ (MA) ህንፃ ላይ በሚገኘው በከተማው መሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ ለዚህ በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡
ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ነሐሴ 13/2017ዓ.ም ከጠዋቱ3፡ዐዐ ሰዓት ጀምሮ ለተከታታይ 3 የስራ ቀናት በቦሌ ክ/ከተማ አስተዳደር አዳራሽ የሚከፈት ሆኖ ዝርዝሩ በውስጥ ማስታወቂያ ይገለፃል፡፡
በተጨማሪ ሐምሌ 22/2017ዓም በአዲስ ልሳን ጋዜጣ በልዩ ዕትም በወጣው ጋዜጣ ላይ ለጨረታ ከቀረቡ ቦታዎች
1ኛ- በአራዳ ክ/ከተማ በወረዳ 06 ለጨረታ ከወጡት ቦታዎች ዉስጥ የቦታ ኮድ LDR-ARA-MIX-00014698፣
LDR-ARA-MIX-00014699 እና
LDR-ARA-MIX-00014700 የቦታ ስፋታቸዉ እንደ ቅደም ተከተላቸዉ 397ሜ.ካ፣ 340ሜ.ካ እና 300ሜ.ካ የሆኑ፣
2ኛ- በጉለሌ ክ/ከተማ የቦታ ኮዳቸዉ
ከ LDR-GUL-MIX-00014660 እስከ GUL-MIX-00014671 ተከታታይ የሆኑ አስራሁለት(12) ቦታዎች
3ኛ- በአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ የቦታ
ኮድ LDR-Aki-MIX-00013630 ስፋት 509ሜ.ካ ከጨረታ የተሰረዙ መሆኑን እና
ቀደም ሲል በቀን 22/11/2017ዓ.ም በልዩ ዕትም በታተመዉ አዲስ ልሳን ጋዜጣ ላይ የጨረታሰነዱን telebirr, M-PESA, CBE birr, Awash Bank, Coop Bank እና Siinqee Bank በመጠቀም መግዛት እንደሚቻል ገልጸን የነበረ ቢሆንም የጨረታ ሰነድ ሽያጩ በቴሌብር( telebirr )ብቻ በመጠቀም መግዛት እንደሚቻል እንገልጻለን፡፡
የጨረታውን ዝርዝር መረጃ ሐምሌ 22/2017ዓ.ም በልዩ ዕትም በወጣው አዲስ ልሣን ጋዜጣ ላይ መመልከት ይቻላል፡፡
መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሠረዝ መብቱየተጠበቀ ነው፡፡
ለተጨማሪ መረጃ የመሬት ልማት አስተዳደር ቢሮ፡-
በስልክ ቁጥር +251111566440 መረጃ ማግኘት ይቻላል፡፡
t.me/addisland
Addis Ababa City Land Development Administration and Bureau
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር
የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.