የቂርቆስ ክፍለ ከተማ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት በዘጠና...

image description
- ክስተቶች News    0

የቂርቆስ ክፍለ ከተማ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት በዘጠና ቀናት ተግባራት በገቢ አሰባሰብ የተሻለ ውጤት ማስመዘገቡን ገለፀ፡፡ (አቶ ሙሉነህ ሙሉጌታ)  ነሀሴ 22/2017 (መልአ)

የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ በተያዘው አዲሱ በጀት ዓመት ከመደበኛ አገልግሎት በተጓዳኛ በ90 ቀናት በትኩረት ሊተገበሩ ይገባል ያላቸውን ዓበይት ተግባራ ለይቶ በዕቅድ እየተመራ ይገኛል፡፡ 

በተጠናቀቀው የ2017 በጀት ዓመት የከተማውን ገፅታ በቀየረው የኮሪደር ልማት ስራዎችና በካብኔ ውሳኔ አፈፃጸም ከፍተኛ ውጤት በማስመዝገብ ዓመቱን በስኬት ማጠናቀቅ የቻለው የቂርቆስ ክፍለ ከተማ መሬት ልማትና አስተዳደር ቅርንጫፍ ፅ/ቤት በበጀት ዓመቱ ዝቅተኛ አፈፃፀም የተመዘገበባቸውን ተግባርት በመለየትና የ90 ቀን የማካካሻ እቅድ አዘጋጅቶ ወደ ስራ መግባቱን የቅንጫፍ ፅ/ቤቱ ኃላፊ ሙሉነህ ሙሉጌታ ተናግረዋል፡፡ 

በዘጠና ቀናት እቅድ 78 ሚሊየን ገቢ እንዲሰበሰብ በቢሮው አቅጣጫ መውረዱን የገለፁት አቶ ሙሉነህ እቅዱን ከሰራተኞች ጋር የጋራ በማድረግ እና ቅዳሜና እሁድን ጨምሮ የቤት ለቤት የቅስቀሳ ስራዎችን በመስራት 97 ሚሊየን ብር ገቢ መሰብሰብ መቻሉን ተናግረዋል ፡፡ ከዚህም 13 ሚሊየኑ በነሀሴ ወር በ21 ቀናት የተሰበሰበ ስለመሆኑም በማከል፡፡ 

በክፍለ ከተማው እየተተገበረ ባለው ሁለተኛ ምዕራፍ የኮሪደር ልማት ቀሪ ተግባራትን በዚሁ በ90 ቀን ዕቅድ በማካተት ለማጠናቀቅ በተሰራው ስራ 713 ሚሊየን ብር የካሳ ክፍያ መፈፀም መቻሉን አንስተዋል፡፡  

ከዚህ ባሻገር 15 ሺህ 200 ቤቶችን በመደዳ በማጥራትና ወደ ጣሪያና ግድግዳ ግብር ተመን ስርአት ያልገቡ 523 ቤቶችን በመለየት ከ29 ሚልዮን ብር በላይ ግብር እንዲከፈል ለገቢዎች ጽ/ቤት የማስተላለፍ ስራ መሰራቱን አውስተው ከአገልግሎት አሰጣጥ ጋር በተያያዘም የመልካም አስተዳደር ችግር የፈጠሩ 18 ሰራተኞች ላይ የእርምት እርምጃ ስለ መወሰዱም አብራርተዋል፡፡ 

ከመደበኛ አገልግሎት በተጓዳኛ በ90 ቀናት ለማሳካት ከታቀዱት አበይት ተግባራት መካከል የአረጋዊያን ቤት እድሳት ፤ የአረንጓዴ አሻራ ፤ ማዕድ ማጋራት እና የደም ልገሳ ኢኒሼቲቭ ስራዎችም ሲተገበሩ እንደነበር ገልጸው በቀሪ ቀናትም የዕቅዱ አካል የሆኑና እስካሁኑ ያልተተገበሩ ተግባራትን የጳጉሜ ወር ከመገባደዱ አስቀድሞ ለማጠናቀቅ ርብርብ ይደረጋል ሲሉ ለቢሮው ኮሙንኬሽን ጉዳዮች ተናግረዋል፡፡


ለበለጠ መረጃ የማህበራዊ ትስስር ገፆቻችንን Like, Follow, subscribe በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ። 
👇👇👇👇👇👇
Face book :-Addis Ababa City Land  Development  Administration and Bureau
Email  ፦addisabababacityland@gmail.com 
Telegram ፦https://t.me/AddisLand
Youtube፦https://www.youtube.com/@AddisAbabaCityLandDevelopment 
Tiktok.https፦//www.tiktok.com/@aa.land.administrator?_t=ZM-8uSveGuoY8T&_r=1
Instagram፥https://www.instagram.com/addisababa


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.