ካለን ማካፈል የኛ መገለጫ ነው የአብሮነታችን ማ...

image description
- ክስተቶች News    0

ካለን ማካፈል የኛ መገለጫ ነው የአብሮነታችን ማሳያ ነዉ።

የፕላን ተግባሪ ተቋማት በጋራ አዲሱን ዓመት ምክንያት በማድረግ ቅን ልብ ካላቸው ወገኖች ባሰባሰቧቸው ሀብት ማዕድ አጋርተዋል።

ጳጉሜ 03/2017ዓ.ም
****
ኢትዮጵያዊያን ካለን ማከፍል የኖርንበት የማንነታችን መገለጫ ነው። 
የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ በዓላትን ያለ ልዩነት ቅን ልብ ካላቸው መስጠትንም ባህል ካደረጉ ወገኖች ሀብት በማሰባሰብ የሀገር ባለውለታዎች እንደሌሎች ሁሉ በዓሉን በደስታ እንዲያሳልፉ ማድረግን ትኩረት የቸረው ተግባሩ ነው። 

የዘንድሮውን አዲስ ዓመት ምክንያት በማድረግ የፕላን ተግባሪ ተቋማት በጋራ ለመስጠት ከተሰጡና ካላቸው በማካፈል ደስታን ከሚያተርፉ በጎ ሰዎች ባሰባሰቡት ሀብት ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይሉ በሙሉ አቅማቸው በተቋማቱ ሲያገለግሉ ቆይተው በጡረታ ለተገለሉ፣ በተቋማቱ ዝቅተኛ ደሞወዝ ለሚከፈላቸው ሰራተኞቻቸውና ለሚያስተምሯቸው ልጆች ማዕድ አጋርተዋል።

በመረሀ ግብሩ ላይ የየተቋማቱ ኃላፊዎች መልዕክት ያስተላለፉ ሲሆን የዘንድሮ የበዓል ዋዜማ እንደ ሀገር  አስደማሚ ተግባሮቻችንን ለዓለም ህዝብ የምናሳይበት መሆኑ ለየት ያደርገዋል ብለዋል የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ አቶ መኮንን ያኢ ። 

እኛ ኢትዮዽያዊን አብሮነት አብሮን የቆየ የጋራ እሴታችን ነው ያሉት ኃላፊው ዛሬ ላይ የተደረገው ማዕድ ማጋራትም አዲሱን ዓመት በደስታ እንዲቀበለው አብሮነትን ይበልጥ ለማጎላት የተሰናዳ ነው በማለት ገልጸዋል። በዓሉ የሰላም የጤናና የብልጽግና ይሆን ዘንድም መልካም ምኞታቸውን ገልፀዋል።


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.