የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮም የግድቡን መጠና...

image description
- ክስተቶች News    0

የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮም የግድቡን መጠናቀቅ አስመልክቶ የተሰማውን ጥልቅ ደስታ በድጋፍ ሰልፍ ገልጿል።

ይቻላል በተግባር የተገለጠበት የኢትዮጵያዊያን የድል ብስራት ነው ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ። 

የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮም የግድቡን መጠናቀቅ አስመልክቶ የተሰማውን  ጥልቅ ደስታ በድጋፍ ሰልፍ ገልጿል። 

መስከረም 4/2018 ዓ.ም
 *’***********
የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ዜጎች ካላቸው ያለስስት በመስጠት መሪዎችም በቅብብሎሽ  በመምራት ለድል ያበቁት የኢትዮጵያዊያን የይቻላል ማሳያ ነው። 

በግድቡ ግንባታ ላይ የነበረን ተሳትፎም በሀገራችን ታራክ በአረንጓዴ ፣ቀይ ቢጫ ቀለም አሻራችንን ያሳረፍንበት የታረክ ባለቤት የሆንበትም ነው።

"በሕብረት ችለናል "በሚል መሪ ቃል በአዲስ አበባ መስቀል አደባባይ ላይ የተደረገው የድጋፍ ሰልፍም  አይችሉም ሲሉን ችለን ለጋራ ዓላማ በአንድ ያበርንበትና ለድል የበቃንበት የታላቁን የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ መጠናቀቁን በማስመልከት የተካሄደ ነው። 

የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ አመራርና ሠራተኞችም በዚህ የድጋፍ ሰልፍ በመሳተፍ የተሰማቸውን ታላቅ ደስታ ገልፀዋል። 

በህዳሴው ግድብ ግንባታ ላይ ያሳየነውን አንድነትና ጥንካሬ በሌሎች ታላላቅ ሀገራዊ ፕሮጀክቶች ላይም ደግመን ሌላ ታራክ እንሰራለን ።


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.