
የዘንድሮው የመስቀልና የኢሬቻ በዓል ትውፊቱን ጠብቆ እንዲከበር የድርሻውን ለመወጣት ዝግጁ መሆኑን የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ ገልፀ።
የቢሮው ሰራተኞች በዚህ ጉዳይ ውይይት አደርገዋል።
መስከረም 09/2018 (መልአ)
********************************
በርካታ ብሔር ብሔረሰቦችና የተለያየ እምነት ተከታዩች በጋራ የሚኖሩባት ልዩነት ውበት ሆኖ የሚደምቅባት ሀገራችን የበርካት ባህልና ተውፊት ባለቤት ናት።
እነኝህም ከቱሪስት መስህቦቻችን ዋነኞች ናቸው። በሀገራችን ኢትዮጲያዊያንን የሚያስተሳስሩ በዓላትም ጥቂት አይደሉም።ከነዚህም በዓላት በመስከረም ወር የሚከበሩ የመስቀልና እሬቻ በዓላት ተጠቃሾች ናቸው ።
የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ ሰራተኞችም የዘንድሮውን የመስቀልና ኢሬቻ በዓላት ምክንያት በማድረግ "በእምርታና ማንሰራራት ህዝባዊ በዓላችንን በጋራ እናክብር" በሚል መሪ ቃል በተሰናዳ ሰነድ ላይ ውይይት አድርገዋል።
ዘንድሮ መስከረም ወር ላይ የተከበሩና የሚከበሩ በዓላት ከወትሮ ለየት ያሉ ናቸው ያሉት የቢሮው ኃላፊ አቶ መኮንን ያዒ ታላቁ የህዳሴ ግድብ መቋጫ አግኝቶ የድል ብስራት የተበሰረበትን በሌላኛው ጫፍ ደግሞ መዲናችንን በብዙ መንገድ ለነዋሪዎቻችን ምቹ የተደረገበትን ኩነት ለአብነት አንስተዋል።
መጭውን የመስቀልና የኢሬቻ በዓላት ስናከብርም ድሎቻችንን ታሳቢ በማድረግ ሊሆን ይገባል በማለትም አክለዋል።
የመወያያ ሰነዱን ያቀረቡት የመብት ፈጠራና ይዞታ አገልግሎት ዘርፍ ምክትል ቢሮ ኃላፊ ኢንጅነር ወንደሰን ባንጃው ከበዓላቶቻችን ጥቂት የማይባሉት በዓለም ቅርስነት የተመዘገቡ የቱሪስት መስህቦቻችን ስለመሆናቸው አውስተዋል።
በዓላቱ ቱፊታቸውን ጠብቀው እንዲከበሩ ፣ ወንድማማችነትና እህማማችነትን በማጠናከርና የእንግዳ ተቀባይነታችንን በማጉላት በሰላም ተክብረው እንዲያልፉ የድርሻችንን መወጣት ይኖርብና ብለዋል።በቀረበው ሰነድ ላይ በተደረገው ውይይትም በዓላቱ ከእኛ አልፎ በዩኒስኮ ላይ የተመዘገቡ የጋራ በዓላቶቻችን በመሆናቸው ለሠላም ትኩረት ሠጥተን በጋራ ማክበር ይኖርብናል ተብሏል።
ኢንጅነር ወንደሰን ባንጃው በማጠቃለያ ሃሳባቸው የመስቀልም ሆነ የእሬቻ በዓል በህዝብ መካከል አንድነትን እና ሕብረብሔራዊነትን የሚያጎለብቱ በመሆናቸው በሰላም እንዲከበሩ ለማድረግ እንደ ተቋም ግንባር ቀደም ሁነን ከህብረተሰቡ ጋር በቅንጅት ልንሰራ ይገባል በማለት ተናግረዋል።
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.