7ውኛ ዙር የመሬት ሊዝ ጨረታ ተራዝሟል

image description
- ክስተቶች News    0

7ውኛ ዙር የመሬት ሊዝ ጨረታ ተራዝሟል

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ ለ7ኛዉ ዙር የመሬት ሊዝ ጨረታ በየካ ፣ንፋስ ስልክ ላፍቶ፤ ኮልፌ ቀራንዮ፣ አቃቂ ቃሊቲ፤ አዲስ ከተማ፣ ለሚ ኩራ፣ ጉለሌ እና ቦሌ ክ/ከተሞች የሚገኙና ለተለያዩ አገልግሎቶች የተዘጋጁ ቦታዎችን በጨረታ አወዳድሮ በሊዝ ለማስተላለፍ ጥቅምት 01/2018 ዓ.ም በአዲስ ልሣን ጋዜጣ በማሳተም ከጥቅምት 03/2018 ዓ.ም እስከ ጥቅምት 14/2018 ዓ.ም ድረስ የሚቆይ የጨረታ ሰነድ ሽያጭ እያከናወነ መሆኑ ይታወቃል፡፡

ይሁን እንጅ የጨረታ ሰነድ ሽያጩን ማራዘም አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ ከጥቅምት17/2018 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ጥቅምት 28/2018 ዓ.ም ከቀኑ 9፡00 ሰዓት ድረስ ለ10 ተከታታይ የስራ ቀናት የጨረታ ሰነድ ሽያጩ የተራዘመ መሆኑን እየገለጽን፡-

ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ለማግኘት የቴሌ ብር አካዉንት በመክፈት ከአካዉንታችሁ ተቀናሽ በማድረግ ክፍያ በመፈጸም የጨረታ ሰነዱን በኦን ላይን በ landleasedocument.aalb.gov.et: በመግባት መግዛትና ሰነዱን ፕሪንት በማድረግ መወዳደር ይኖርባቸዋል፡፡

የጨረታ ሰነድ ግዢውን እስከ ጥቅምት 28/2018 ዓ.ም ከቀኑ 9፡00 ሰዓት ድረስ የተራዘመ በመሆኑ ቦታዎቹን በእነዚሁ ቀናት በስራ ሰአት ጠዋት 3፡00 ሰአት እና ከሰአት 8፡00 ሰአት በየክፍለ ከተማዉ የመሬት ልማትና አስተዳደር ቅ/ጽ/ቤት በመገኘት መጎብኘት የሚቻል መሆኑን እየገለጽን

ተጫራቾች የጨረታ መልስ ማቅረቢያ ሰነድ፣ ሲፒኦ፣የግንባታ አቅም ማሳያ ማስረጃ፣ሰነዱን ለመግዛት በቴሌ ብር የከፈሉበት ስሊፕ፣መታወቂያ እና ሌሎች መያያዝ ያለባቸዉና በተጫራቾች መመሪያ ላይ የተገለጹትን በመጨመር እና ሰነዶችን ኮፒ በማድረግ ዋናዎቹን(ኦርጂናል) መረጃዎች በአንድ (1) ኤንቨሎፕ በማሸግ ኮፒዎችንም በሌላ አንድ(1) ኤንቨሎፕ በማሸግ በሁለቱም ኤንቨሎፕ ላይ ተጫራቹ ሙሉ ስሙን የተወዳደረበትን የቦታ ኮድ እና የጨረታ ቁጥር በመፃፍ  ሁለቱንም ኤንቨሎፖች በሌላ አንድ (1) ኤንቨሎፕ በማሸግና  ተጫራቹ ሙሉ ስሙን የተወዳረበትን የቦታ ኮድ እና የጨረታ ቁጥር  በመፃፍ  ጥቅምት 28/2018 ዓ.ም ከቀኑ 11፡30 ሰዓት ድረስ ለም ሆቴል አከባቢ ኤም ኤ (MA) ህንፃ ላይ በሚገኘው በከተማው መሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ ለዚህ በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡ ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ሰኞ ህዳር 01/2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡ዐዐ ሰዓት ጀምሮ ለተከታታይ ቀናት በቦሌ ክ/ከተማ አስተደዳር አዳራሽ የሚከፈት ሆኖ ዝርዝሩ በውስጥ ማስታወቂያ ይገለፃል፡፡

የጨረታውን ዝርዝር መረጃ ጥቅምት 01 ቀን 2018 ዓ.ም በወጣው አዲስ ልሣን ጋዜጣ ላይ መመልከት ይቻላል፡፡

መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ለተጨማሪ መረጃ የመሬት ልማት አስተዳደር ቢሮ፡-

ስልክ ቁጥር +251111570595 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡

 

የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ

 

 


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.