እምርታ የሚሻውን ጊዜና እውቀት ተጠቅመን በፍጥነት የታጀበ ጥራት ያለው አገልግሎት ልንሰጥ ይገባል ። አቶ መኮንን ያኢ
የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ የእምርታ ግቦች እቅድ አፈፃፀም ላይ ውይይት አድርጓል።
ህዳር 28/2018(መልአ)
***
የእምርታ ግቦች እቅድ በተቋሙ ዋና ዋና የትኩረት መስኮች ተብለው በተለዩ ተግባራት ላይ ያተኮረ ነው።
የእምርታ ግብ ጊዜንና ወጭን በመቆጠብ ፈጣንና ጥራት ያለው አገልግሎት በመስጠት ውጤት ማምጣትን የሚሻ በመሆኑ እንደ ተቋም ባለሙያው ወደራሱ ወስዶ እንዲተግብር እየተደረገ ነው።
በእቅድ አፈፃፀም ውይይቱ ላይ እንደተመላከተው የመልካም አስተዳደርና ቅሬታ አፈታት ተግባር የአንድ ማዕከል አገልግሎት አሰጣጥን ተከትሎ ውጤታማ የተሆነበት ሌሎች ተቋማትም ልምድ የቀመሩበትና እውቅና የሰጡበትም ነበር።
የልማት ተነሽዎች መስተንግዶ ፣መብት ፈጠራ፣የሊዝ ገቢ አሰባሰብ፣ የግንባታ ክትትል፣የአገልግሎት ለውጥ ህግ ማስከበርና ታጥሮ የተቀመጡ ቦታዎች ጋር በተያያዘ ከባለፉት ወራት አፈፃፀም አንፃር ውስንነት የነበረበት እንደነበርም ተነስቷል።
ለዚህም በምክንያትነት የቀረቡ ጉዳዮች ቢኖሩም እምርታ የሚሻውን ጊዜያችንን እና እውቀታችንን ተጠቅመን ትኩረት እንዲሰጥባቸው በተለዩ ተግባራት ላይ በፍጥነት የታጀበ ጥራት ያለው አገልግሎት ልንሰጥ ይገባል ብለዋል የቢሮው ኃላፊ አቶ መኮንን ያኢ።
ብልሹ አሰራርን ለመከላከልም እየተወሰደ ያለው እርምጃ አስተማሪ ሊሆን ይገባል ተግባሩን ለማስቆምም መጋፈጥ ይኖርብናል በማለት አክለዋል።
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.