ክስተቶች

ክስተቶች Event

image description
የመጀመሪያ ቀን icon
የመጨረሻ ቀን icon
አካባቢ የአዲስ አበባ መሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ

ቢሮው “የአገልግሎት ልህቀት ለሴክተሩ ማንሰራራት” በሚል ርዕስ የማነቃቂያ ውይይት አካሄደ። 

መስከረም 12/2018 (መልአ) 

የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ በወርቃማው ሰኞ “የአገልግሎት ልህቀት ለሴክተሩ ማንሰራራት” በሚል ርዕስ የማነቃቂያ ውይይት አካሂዷል፡፡ 

ኢትዮጵያ የማንሰራራት ዘመን ላይ ናት ያሉት የውይይት ሰንድ አቅራቢው ዶ/ር ኢንጂነር እሸትአየሁ ክንፉ የዚህ ዘመን መገለጫዎች መካከል የአባይ ግድብ ዋነኛው ነው ብለዋል። ግድቡን ለመገንባት ባደረግነው ጥረት ልክ፣  የተሳለጠና የላቀ አገልግሎት በመስጠት ለኢኮኖሚው ዕድገት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ማበርከት አለብን ሲሉም በማከል። 

ደንበኛ ተኮር አገልግሎት መስጠት፣ ቀጣይነት ያለው መሻሻል፣ መፍጠርና መማር፣ ጥራትና ውጤታማነት እንዲሁም መልካም የስራና የአመራር ባህል መፍጠር እንደሚገባም ገልፀዋል፡፡ 

በውይይቱ ላይ ተሳታፊ የነበሩ ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶችም  አገልግሎት አሰጣጥን ይበልጥ ለማጠናከር፣ ራስን እያበቁ መሄድና ለደንበኞች ፍትሃዊ አገልግሎት መስጠት እንደሚገባ ጠቁመው ለግድቡ ግንባታ ከነበረን ቁርጠኝነት አንፃር የአገልግሎት አሰጣጥን ማሻሻል ከባድ አይሆንብንም ሲሉም እምነታቸውን ገልጸዋል። 

የጊዜ አጠቃቀምን ማሻሻልና ወርቃማ ሰኞን ይበልጥ ውጤታማ ማድረግ አስፈላጊ መሆኑን ያስገነዘቡት የቢሮው ኃላፊ አቶ መኮንን ያኢ የአባይ ግድብ ግንባታ ለተቋሙ ሰራተኞች የይቻላል መንፈስ መለኪያ እንደሆነ አጽንኦት ሰጥተው በሳምንቱ በትኩረት መከናወን ያለባቸውን ያደሩ ገቢዎችን መሰብሰብ፣ የአርሶ አደር መብት ፈጠራ እና የኢ-ካርታ አገልግሎት ስራን መቋጨት  ይገባል ብለዋል።

ለበለጠ መረጃ የማህበራዊ ትስስር ገፆቻችንን Like, Follow, subscribe በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ። 
👇👇👇👇👇👇
Face book :-Addis Ababa City Land  Development  Administration and Bureau
Email  ፦addisabababacityland@gmail.com 
Telegram ፦https://t.me/AddisLand
Youtube፦https://www.youtube.com/@AddisAbabaCityLandDevelopment 
Tiktok.https፦//www.tiktok.com/@aa.land.administrator?_t=ZM-8uSveGuoY8T&_r=1
Instagram፥https://www.instagram.com/addisababa

  • icon 9:30am - 1:00pm
  • የአዲስ አበባ መሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ

Related Events