
የመጀመሪያ ቀን
icon
የመጨረሻ ቀን
icon
አካባቢ
የአዲስ አበባ መሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ
ችግኝ እንተክላለን፤ ተንከባከብንም የጽድቀት መጠኑን እናሳድጋለን" (የመብት ፈጠራና ይዞታ አገልግሎት ዘርፍ አመራርና ሠራተኞች)
መስከረም 10/2018 (መልአ)
በመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ የመብት ፈጠራና ይዞታ አገልግሎት ዘርፍ አመራርና ሠራተኞች "ችግኝ እንተክላለን፤ ተንከባከብንም የጽድቀት መጠኑን እናሳድጋለን" በሚል መሪ ቃል የችግኝ ኩትኳቶና እንክብካቤ አደረገዋል።
የመብት ፈጠራና ይዞታ አገልግሎት ዘርፍ ምክትል ቢሮ ኃላፊ ኢንጂነር ወንዶሰን ባንጃው በአገራችን የታሠበውን የአረንጓዴ አሻራ ዕቅድ ከግብ ለማድረስ ችግኝ መትከል ብቻ ሳይሆን አድገው ለፍሬ እንዲበቁ ልንከባከባቸው ይገባል ብለዋል።
የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ እንደ ሀገር ተግባራዊ እየሆነ ባለው የአረንጓዴ አሻራ መረሀ ግብር በመሳተፍ ችግኞችን ከመትከል ባለፈ የጽድቀት መጠናቸውን ለማሳደግ የመንከባከቡን ተግባር ከማዕከል እስከ ቅርንጫፍ ጽቤቶቸ እያከናወነ ይገኛል።