
value="
ፕሬስ ሪሊዝ
የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ 7ኛ ዙር የመሬት ሊዝ ጨረታ ለማውጣት ዝግጅቱን አጠናቋል፡፡ አቶ ክብሮም አሰፋ
መስከረም 28/2018 (መልአ)
**********
አሰራርን በማዘመን የተገልጋይ እርካታን ማረጋገጥ የዕለት ተዕለት ተግባሩ ያደረገው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር መሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ 7ኛ ዙር የመሬት ሊዝ ጨረታ ለማውጣት ዝግጅት ማጠናቀቁን የጨረታ ኮሚቴው አስተባባሪ አቶ ክብሮም አሰፋ ለቢሮው ኮሙንኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ተናግረዋል፡፡
በበጀት ዓመቱ ለ2ኛ ጊዜ በተሰናዳው 7ኛ ዙር የመሬት ሊዝ ጨረታ በ8 ክፍለ ከተሞች 384 ፕሎቶችን ከፕላን ተቃርኖ እና ከሶስተኛ ወገን ነፃ በማድረግ በቅርቡ ለምቶ ስራ ላይ በዋለው የተቋሙ ድረ-ገፅ (https://www.lndleasedocument .aalb.gov.et) ከጥቅምት 3/2018 እስከ ጥቅምት 14/2018 ዓ.ም ባሉት ተከታታይ የስራ ቀናት እስከ ቀኑ 9:00 ድረስ ብቻ በኦንላይን የሰነድ ሽያጭ እንደሚካሄድ ተመላክቷል ፡፡
በዚህ መሰረት በጨረታው መሳተፍ የሚፈልግ ኢትዮጵያዊ በቦታ እና በጊዜ ሳይወሰን ባለበት ቦታ ሆኖ የጨረታ ሰነዱን በቴሌ ብር ክፍያ በመፈፀም በኦንላይን በመግዛት መወዳደር ይችላል፡፡
ተጫራቾች የጨረታውን ዝርዝር መረጃ ጥቅምት 01/2018 ዓ.ም በሚወጣው አዲስ ልሳን ጋዜጣ መመልከት ይችላሉ፡፡የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ በ6ኛ ዙር የመሬት ሊዝ ጨረታ 132 ፕሎቶችን በሊዝ አወዳድሮ ለአልሚዎች ማስተላለፉ ይታወሳል፡፡
ለበለጠ መረጃ የማህበራዊ ትስስር ገፆቻችንን Like, Follow, subscribe በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ።
👇👇👇👇👇👇
Face book :-Addis Ababa City Land Development Administration and Bureau
Email ፦addisabababacityland@gmail.com
Telegram ፦https://t.me/AddisLand
Youtube፦https://www.youtube.com/@AddisAbabaCityLandDevelopment
Tiktok.https፦//www.tiktok.com/@aa.land.administrator?_t=ZM-8uSveGuoY8T&_r=1
Instagram፥https://www.instagram.com/addisababa
"