የመጀመሪያ ቀን
icon
የመጨረሻ ቀን
icon
አካባቢ
የአዲስ አበባ መሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ በንፋስ ስልክ ላፍቶ ፣ በኮልፌ ቀራንዮ ፣ በአቃቂ ቃሊቲ ፣ በየካ ፣ በአዲስ ከተማ፣ በቂርቆስ ፣ በጉለሌ እና በለሚ ኩራ ክ/ከተሞች የሚገኙ ለተለያዩ አገልግሎቶች የተዘጋጁ ቦታዎችን በጨረታ አወዳድሮ በሊዝ ለማስተላለፍ ታህሳስ 25 ቀን 2018 ዓ.ም በአዲስ ልሳን ጋዜጣ ማውጣቱና ከየካቲት 09 ቀን 2018ዓ.ም ጀምሮ አንደኛ
አሸናፊዎች ጥሪ ተደርጎላቸዉ የሚበዙት የሊዝ ዉል የተዋዋሉ መሆኑ ይታወቃል፡፡
በመሆኑም የቦታ ኮዳቸው ከዚህ በታች የተገለጸ የሊዝ ቦታዎች አንደኛ እና ሁለተኛ የወጡ ተጫራቾች ውል ስላልፈጸሙባቸው በሊዝ ደንብ ቁጥር 162/2016 አንቀፅ 25 ንዑስ አንቀፅ 6 መሰረት ሶስተኛ የወጣችሁና ስማችሁ ከቦታ ኮዱ ጋር የተገለጸ ተጫራቾች አንደኛ አሸናፊ ባቀረበዉ ዋጋ እና ቅድመ ክፍያ በመክፈል መዋዋል የምትፈልጉ ከሆነ ከቀን 13/07/2018ዓ.ም ጀምሮ ባሉት 10/አስር/ ተከታታይ የስራ ቀናት በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሂሳብ ቁጥር 1000004337631 ቅድመ ክፍያዉን ገቢ በማድረግና የከፈላችሁበትን የባንክ ስሊፒ በመያዝ በመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ ቀርባችሁ የሊዝ ዉል መዋዋል የምትችሉ መሆኑን እናሳዉቃለን፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር
የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ