ክስተቶች

ክስተቶች Event

image description
የመጀመሪያ ቀን icon
የመጨረሻ ቀን icon
አካባቢ የአዲስ አበባ ከተማ መሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ

ሀምሌ 03/2018 (መልአ)
**********

በህጋዊ መንገድ የተፈፀሙ የይዞታ ግዥዎች በአስቸኳይ የስመ ንብረት ዝውውር እንዲደረጉ በድጋሚ ጥሪ ቀረቧል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ መሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ ሰኔ 09 ቀን 2018 ዓ.ም በተለያየ ጊዜ በህጋዊ መንገድ የተፈፀሙ የይዞታ ግዥዎች የስመ-ንብረት ዝውውር እንዲደረግ ባስቀመጠው አስቀጣጫ መሰረት ለበርካታ የህብረተሰብ ክፍሎች የስመ-ንብረት�ዝውውርና የይካተትልኝን ጨምሮ ቀልጣፋ የመደበኛ አገልግሎት መስተንግዶ እየተሰጠ እንደሚገኝ የይዞታ ማስተካከል ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ተስፋሚካኤል እንዳለ ተናግረዋል፡፡

በውልና ማስረጃ ግዥ ፈፅመው የስመ ንብረት ዝውውር ያላደረጉ ዜጎች በሚኖሩበት ክፍለ ከተማ ቢሮው ባመቻቸው የኦንላይን አገልግሎት በማመልከት እስከ ጳጉሜ 5/2018 ዓ.ም ስመ በማዞር የንብረት ባለቤትነት ዋስትናቸውን እንዲያረጋግጡ ዳይሬክተሩ በድጋሚ ጥሪ አቅርቧል፡፡

በተቋም ደረጃ በተዘጋጀው የ90 ቀን ንቅናቄ በየደረጃው ከሚሰጡ መደበኛ የይዞታ አገልግሎቶች 660 ሚሊየን ብር ለመሰብሰብ መታቀዱን ያስታወሱት አቶ ተስፋሚካኤል በሰኔ ወር ብቻ ከ426 ሚሊየን 960ሺ ብር በላይ ገቢ መገኘቱን ተናግረዋል፡፡

ጨምረውም በቀጣይ 30 ቀናት የስመ-ንብረትና ኢ-ካርታ አገልግሎትን ጨምሮ ከሌሎች የመደበኛ ይዞታ አገልግሎት 500ሚሊየን ብር ለመሰብሰብ መታቀዱን ለቢሮው ኮሙንኬሽን ዳይሬክቶሬት. አሳውቀዋል፡፡

ለበለጠ መረጃ ትስስር ገፆቻችንን Like, Follow, subscribe በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ።
👇👇👇👇👇👇
https://linktr.ee/addisabababacityland

"

  • icon 9:30am - 1:00pm
  • የአዲስ አበባ ከተማ መሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ

Related Events

image description
Event

  • የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ
ተጨማሪ ዝርዝሮች
image description
Event

  • በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር መሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ
ተጨማሪ ዝርዝሮች