ሰኔ 25/2018/መልአ/
****
የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ በ8ኛ ዙር የአረንጓዴ አሻራ ንቅናቄ ከማዕከል እስከ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ከ11ሺ በላይ ሀገር በቀል ችግኞችን ለመትከል ታቅዶ ወደ ተግባር ተገብቷል።
መርሐ ግብሩ ሰኔ 21/2018 ዓ.ም በየደረጃው በሚገኙ የማዕከልና ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ከፍተኛ እና መካከለኛ አመራሮች 520 ችግኞች በመትከል በይፋ የተጀመረ ሲሆን በዛሬው እለትም የማዕከል አመራርና ሰራተኞች በቦሌ ክፍለ ክፍለ ከተማ ወረዳ አንድ ከ3ሺ በላይ ሀገር በቀል ችግኞችን ተክለዋል።
መርሐ ግብሩን ያስጀመሩት የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ አቶ መኮንን ያኢ ኢትዮጵያ ባለፉት ሰባት የለውጥ ዓመታት አሳሳቢ የሆነውን የአየር ንብረት ለውጥ ለመከላከል ለአረንጓዴ ልማት ባደረገችው ልዩ ትኩረት ከ48 ቢሊየን በላይ ችግኞች መትከሏን አስታውሰው ፤በሀገር አቀፍ ደረጃ ለአየር ንብረት ለውጥ የማይገበር የአረንጓዴ ኢኮኖሚ ለመገንባት በሚደረገው እንቅስቃሴ የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ ሰራተኞችም ኃላፊነታቸውን በሚገባ መወጣታቸውን ተናግረዋል።
በቀጣይም ሀገሪቱ የያዘችው የአረንጓዴ አሻራ ውጥን እውን እንዲሆን በተቋም ደረጃ የእቅዳችን አንድ አካል አድርገን እንሰራለን በማለት
የተተከሉትን ችግኞች እስኪፀድቁ ድረስ አስፈላጊው እንክብካቤ እንዲደረግ አሳስበዋል ።
ለበለጠ መረጃ የትስስር ገፃችንን Like, Follow, subscribe በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ።
👇👇👇👇
https://linktr.ee/addisabababacityland