የመጀመሪያ ቀን
icon
የመጨረሻ ቀን
icon
አካባቢ
የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ ለም ሆቴል
ሰኔ 27/2018 (መልአ)
***
በ90 ቀን ልዩ ዕቅዱ ሰው ተኮር ተግባራትን አካቶ ወደ ስራ የገባው የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ በአረንጓዴ አሻራ መረሐ ግብር ከ11 ሽህ በላይ ችግኞችን መትከል ከውጥኑ አንዱ ነው ።
በዚህም ቢሮው በማዕከል ደረጃ 3ሺህ ችግኞችን በመትከል ንቅናቄው በቅርንጫፎችም ተግባራዊ እንዲሆን አድርጓል ።
በዛሬው ዕለትም የአቃቂ ቃሊት ቅርንጫፍ ጽ/ቤት 1 ሺህ 500 ሀገር በቀል ችግኞችን በመትከል የድርሻዉን ተወቷል።
ሀገሪቱ የያዘችው የአረንጓዴ አሻራ ውጥን እውን እንዲሆን በተቋም ደረጃ የእቅዳቸው አንድ አካል አድርገው እንደሚሰሩ የገለፁት የቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ኃላፊ ወ/ሮ ትዕግስት አበራ የተተከሉ ችግኞች እስኪፀድቁ ድረስም ተገቢው እንክብካቤ ይደረጋል ብለዋል።