የአበባ ከተማ አስተዳደር የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ የ5ኛ ዙር የመሬት ሊዝ ጨረታ አሸናፊዎች ዝርዝር ማስታወቂያ
የአበባ ከተማ አስተዳደር የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ የ5ኛ ዙር የመሬት ሊዝ ጨረታ አሸናፊዎች ዝርዝር ማስታወቂያ
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ ፣ በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከተማ፤ በኮልፌ ቀራንዮ፣ በአቃቂ ቃሊቲ፣ በየካ፣ በአዲስ ከተማ ፣ በጉለሌ፣ ቂርቆስ፣እና በለሚ ኩራ ክ/ከተሞች የሚገኙ ለተለያዩ አገልግሎቶች የተዘጋጁ የልማት ቦታዎችን በጨረታ አወዳድሮ በሊዝ ለማስተላለፍ የካቲት 29 ቀን 2017 ዓ.ም በአዲስ ልሳን ጋዜጣ ማውጣቱና ከመጋቢት 29 ቀን 2017 ዓ.ም እስከ ሚያዝያ 03 ቀን 2017 ዓ/ም ድረስ በይፋ ተከፍቶ አሸናፊዎች መለየታቸው ይታወቃል፡፡
በዚሁ መሠረት ስማችሁ ከዚህ በታች በተዘረዘረዉ አግባብ 1ኛ የወጣችሁ አሸናፊ ተጫራቾች ይህ ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ ባሉት አስር (10) ተከታታይ የሥራ ቀናት ዉስጥ ለም ሆቴል አካባቢ ኤም.ኤ ህንጻ ላይ በሚገኘው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ 3ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 303 በመቅረብ የሊዝ ዉል እንድትፈጽሙ ጥሪያችንን እያስተላለፍን አንደኛ ተጫራቾች ዉል የማይፈጽሙ ከሆነ በደንቡ መሰረት ዕድሉ 2ኛ ለወጡ ተጫራቾች የሚሰጥ በመሆኑና 2ኛ የወጡ ተጫራቾች በተመሳሳይ ዉል የማይፈጽሙ ከሆነ 3ኛ የወጡ ተጫራቾች በሊዝ ደንብ 162/2016 እና በተጫራቾች መመሪያ ላይ በተቀመጠው የጊዜ ሰሌዳ መሰረት በውስጥ ማስታወቂያ ጥሪ የምናደረግ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር
የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ