የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ የ6ኛ ዙር የመሬት ሊዝ ጨረታ አሸናፊዎች ዝርዝር
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ የ6ኛ ዙር የመሬት ሊዝ ጨረታ አሸናፊዎች ዝርዝር
ማስታወቂያ
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ በየካ፣በኮልፌ ቀራንዮ፣በአዲስ ከተማ፣በጉለሌ፣በለሚ ኩራ፣በአቃቂ ቃሊቲ እና በን/ስ/ላፍቶ ከ/ከተሞች የሚገኙ ለተለያዩ አገልግሎቶች የተዘጋጁ የልማት ቦታዎችን በጨረታ አወዳድሮ በሊዝ ለማስተላለፍ ሐምሌ 22 ቀን 2017ዓ.ም በአዲስ ልሳን ጋዜጣ ማስታወቂያ ማዉጣቱና ከነሐሴ 13 ቀን 2017ዓ.ም እስከ ነሐሴ 15 ቀን 2017ዓ.ም ድረስ በይፋ ተከፍቶ አሸናፊዎች መለየታቸዉ ይታወቃል፡፡
በዚሁ መሰረት ስማችሁ ከዚህ በታች በተዘረዘረዉ አግባብ 1ኛ የወጣችሁ አሸናፊ ተጫራቾች ይህ ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ባሉት አስር(10) የስራ ቀናት ዉስጥ ለም ሆቴል አካባቢ ኤም.ኤ.ህንጻ ላይ በሚገኘዉ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ 3ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 303 በመቅረብ የሚጠበቅባችሁን በማሟላት የሊዝ ዉል እንድትፈጽሙ ጥሪያችንን እያስተላለፍን አንደኛ ተጫራቾች ዉል የማይፈጽሙ ከሆነ በሊዝ ደንቡ መሰረት ዕድሉ 2ኛ ለወጡ ተጫራቾች የሚሰጥ በመሆኑና 2ኛ የወጡ ተጫራቾችም በተመሳሳይ ዉል የማይፈጽሙ ከሆነ 3ኛ የወጡ ተጫራቾች በሊዝ ደንብ 162/2016 እና በተጫራቾች መመሪያ ላይ በተቀመጠዉ የጊዜ ሰሌዳ መሰረት በዉስጥ ማስታወቂያ ጥሪ የምናደርግ መሆኑን እየገለጽን ለጨረታ ከወጡ 132 ቦታዎች ዉስጥ የቦታ ኮድ LDR-NIF-MIX-00014508 ከጨረታ የተሰረዘ መሆኑን እናሳዉቃለን፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር
የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ