ህትመቶች

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ የ7ኛ ዙር የመሬት ሊዝ ጨረታ  አሸናፊዎች ዝርዝር

  የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ የ7ኛ ዙር የመሬት ሊዝ ጨረታ  አሸናፊዎች ዝርዝር

               ማስታወቂያ         

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ በየካ፣በኮልፌ ቀራንዮ፣በአዲስ ከተማ፣በጉለሌ፣በለሚ ኩራ፣በአቃቂ ቃሊቲ እና በን/ስ/ላፍቶ ከ/ከተሞች የሚገኙ ለተለያዩ አገልግሎቶች  የተዘጋጁ የልማት ቦታዎችን በጨረታ አወዳድሮ በሊዝ ለማስተላለፍ ጥቅምት 01 ቀን 2018ዓ.ም በአዲስ ልሳን ጋዜጣ ማስታወቂ ማዉጣቱና ከህዳር 01 ቀን 2018ዓ.ም እስከ ህዳር 05 ቀን 2018ዓ.ም ድረስ በይፋ ተከፍቶ አሸናፊዎች መለየታቸዉ ይታወቃል፡፡

በዚሁ መሰረት ስማችሁ ከዚህ በታች በተዘረዘረዉ አግባብ 1ኛ የወጣችሁ አሸናፊ ተጫራቾች ይህ ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት አስር(10) ተከታታይ የስራ ቀናት ዉስጥ ለም ሆቴል አካባቢ ኤም.ኤ.ህንጻ ላይ በሚገኘዉ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ 3ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 303 በመቅረብ የሚጠበቅባችሁን በማሟላት የሊዝ ዉል እንድትፈጽሙ ጥሪያችንን እያስተላለፍን አንደኛ የወጡ ተጫራቾች ዉል የማይፈጽሙ ከሆነ በሊዝ ደንቡ መሰረት አንደኛ የወጣዉ ተጫራች በሰጠዉ ዋጋ ዕድሉ 2ኛ ለወጡ ተጫራቾች የሚሰጥ በመሆኑና 2ኛ የወጡ ተጫራቾችም በተመሳሳይ ዉል የማይፈጽሙ ከሆነ 3ኛ የወጡ ተጫራቾች አንደኛ የወጣዉ ተጫራች በሰጠዉ ዋጋ እንዲዋዋሉ በሊዝ ደንብ 162/2016 እና በተጫራቾች መመሪያ ላይ በተቀመጠዉ የጊዜ ሰሌዳ መሰረት በዉስጥ ማስታወቂያ ጥሪ የምናደርግ መሆኑን እየገለጽን ለጨረታ ከወጡ 224 ቦታዎች ዉስጥ የቦታ ኮድ LDR-LIMK-MIX-00014764 ፣ LDR-Aki-MIX-00014894 ፣ LDR-Aki-MIX-00014903 ፣ LDR-Aki-MIX-00014925 ፣ LDR-NIF-MIX-00015061 ፣ LDR-YEKA-MIX-00014954 ፣ LDR-YEKA-MIX-00014955 ፣ LDR-KOL-MIX-00015006 ከጨረታ የተሰረዙ መሆኑን እናሳዉቃለን፡፡