ማስታወቂያ
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ በ7ኛ ዙር የመሬት ሊዝ ጨረታ በ7 ክፍለ ከተሞች የሚገኙና ለተለያዩ አገልግሎቶች የተዘጋጁ የልማት ቦታዎችን በጨረታ አወዳድሮ በሊዝ ለማስተላለፍ ጥቅምት 01 ቀን 2018 ዓ.ም በአዲስ ልሳን ጋዜጣ በማውጣት ከህዳር 01 ቀን 2018ዓ.ም እስከ ህዳር 05 ቀን 2018 ዓ/ም ድረስ በይፋ ተከፍቶ አሸናፊዎች መለየታቸው ይታወሳል። ይህን ተከትሎ አሸናፊዎች በተቋማችን በመቅረብ የሊዝ ዉል እንድትፈጽሙ ህዳር 20 ቀን 2018ዓ.ም በአዲስ ልሳን ጋዜጣ ጥሪ ባስተላለፍነው መሰረት በሊዝ ደንብ ቁጥር 162/2016 በተቀመጠው የአስር ቀን ገደብ ውስጥ በርካታ የሊዝ ጨረታ አሸናፊዎች ቢሮ ቀርበው የሊዝ ዉል ፈጽመዋል፡፡
ይሁን እንጂ ስማችሁ ከዚህ በታች የተገለጸ የመሬት ሊዝ ጨረታ አሸናፊዎች በደንቡ መሰረት በተቀመጠው የጊዜ ገደብ ቀርባችሁ ውል አልፈፀማችሁም።
በመሆኑም የሊዝ ደንብ ቁጥር 162/2016 አንቀጽ 25 ንኡስ አንቀፅ 4 በግዜ ገደብ ዉል ያልፈፀሙ አንደኛ የወጡ አሸናፊ ተጫራቾች በሶስት ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ቀርበው ውል እንዲፈጽሙ የማስጠንቀቂያ ጊዜ እንዲሰጣቸው በሚደነግገው መሰረት ከ06/04/2018ዓ.ም እስከ 08/04/2018 ባሉት 3/ሶስት/ ተከታታይ የስራ ቀናት ቀርባችሁ የሊዝ ዉል እንድትፈጽሙ እያሳሰብን ይህ ሳይሆን ቢቀር በሊዝ ደንብ ቁጥር 162/2016 አንቀጽ 25 ንኡስ አንቀፅ 5 መሰረት አሸናፊነታችሁ ተሰርዞ ያስያዛችሁት የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ ለመንግስት ገቢ በማድረግ ሁለተኛ ለወጡ ተጫራቾች እድሉ የሚሰጥ መሆኑን እናሳዉቃለን፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር
የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ
ታህሳስ 04/2018ዓ.ም