ማስታወቂያ
ቀን፡- 09/04/2018ዓ.ም
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ በንፋስ ስልክ ላፍቶ ፣ በኮልፌ ቀራንዮ ፣ በአቃቂ ቃሊቲ ፣ በየካ ፣ በአዲስ ከተማ፣ በጉለሌ እና በለሚ ኩራ ክ/ከተሞች የሚገኙና ለተለያዩ አገልግሎቶች የተዘጋጁ ቦታዎችን በጨረታ አወዳድሮ በሊዝ ለማስተላለፍ ጥቅምት 01 ቀን 2018ዓ.ም በአዲስ ልሳን ጋዜጣ ማውጣቱና ከህዳር 20ቀን 2018ዓ.ም ጀምሮ አንደኛ አሸናፊዎች ጥሪ ተደርጎላቸዉ የሊዝ ዉል እዲዋዋሉ መደረጉ ይታወቃል፡፡
ግን ደግሞ የቦታ ኮዳቸው ከዚህ በታች የተገለጸ የሊዝ ቦታዎች አንደኛ የወጡ ተጫራቾች ውል ስላልፈጸሙባቸው በሊዝ ደንብ ቁጥር 162/2016 አንቀፅ 25 ንዑስ አንቀፅ 6 መሰረት ሁለተኛ የወጣችሁና ስማችሁ ከቦታ ኮዱ ጋር የተገለጸ ተጫራቾች አንደኛ አሸናፊ ባቀረበዉ ዋጋ ቅድመ ክፍያ በመክፈል መዋዋል የምትፈልጉ ከሆነ ከታህሳስ 09 ቀን 2018ዓ.ም ጀምሮ ባሉት 10/አስር/ ተከታታይ የስራ ቀናት በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሂሳብ ቁጥር 1000004337631 ቅድመ ክፍያዉን ገቢ በማድረግና የከፈላችሁበትን የባንክ ስሊፒ በመያዝ በመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ ቀርባችሁ የሊዝ ዉል መዋዋል የምትችሉ መሆኑን እናሳዉቃለን፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር
የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ