ሶስተኛ የወጣችሁና ስማችሁ ከቦታ ኮዱ ጋር የተገለጸ ተጫራቾች
ቀን፡- 23/04/2018ዓ.ም
ማስታወቂያ
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ በ7 ክፍለ ከተሞች የሚገኙና ለተለያዩ አገልግሎቶች የተዘጋጁ ቦታዎችን በጨረታ አወዳድሮ በሊዝ ለማስተላለፍ ጥቅምት 01 ቀን 2018ዓ.ም በአዲስ ልሳን ጋዜጣ በማውጣትና የጨረታ ሂደቱን ተከትሎ ግልጽ ጨረታ በማካሄድ ከህዳር 20ቀን 2018ዓ.ም ጀምሮ ለአንደኛ አሸናፊዎች ጥሪ ተደርጎላቸዉ አብዛኞቹ የሊዝ ዉል የተዋዋሉ መሆኑ ይታወቃል፡፡
ይሁን እንጂ የቦታ ኮዳቸው ከዚህ በታች የተገለጸ የሊዝ ቦታዎች አንደኛ እና ሁለተኛ የወጡ ተጫራቾች ውል ስላልፈጸሙባቸው በሊዝ ደንብ ቁጥር 162/2016 አንቀፅ 25 ንዑስ አንቀፅ 6 መሰረት ሶስተኛ የወጣችሁና ስማችሁ ከቦታ ኮዱ ጋር የተገለጸ ተጫራቾች አንደኛ አሸናፊ ባቀረበዉ ዋጋ እና ቅድመ ክፍያ በመክፈል መዋዋል የምትፈልጉ ከሆነ ከቀን 23/04/2018ዓ.ም ጀምሮ ባሉት 10/አስር/ ተከታታይ የስራ ቀናት በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሂሳብ ቁጥር 1000004337631 ቅድመ ክፍያዉን ገቢ በማድረግና የከፈላችሁበትን የባንክ ስሊፒ በመያዝ በመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ ቀርባችሁ የሊዝ ዉል መዋዋል የምትችሉ መሆኑን እናሳዉቃለን፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር
የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ