ህትመቶች

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ የ8ኛ ዙር የመሬት ሊዝ ጨረታ አሸናፊዎች ዝርዝር ማስታወቂያ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ በየካ፣ በኮልፌ ቀራንዮ፣ በአዲስ ከተማ፣ በጉለሌ፣ በለሚ ኩራ፣ በአቃቂ ቃሊቲ፣ በን/ስ/ላፍቶ እና በቂርቆስ ክ/ከተሞች የሚገኙ ለተለያዩ አገልግሎቶች የተዘጋጁ የልማት ቦታዎችን በጨረታ አወዳድሮ በሊዝ ለማስተላለፍ ታህሳስ 25 ቀን 2018ዓ.ም በአዲስ ልሳን ጋዜጣ ማስታወቂያ ማውጣቱ ይታወቃል፡፡ በዚሁ መሰረት ስማችሁ ከዚህ በታች በተዘረዘረዉ አግባብ 1ኛ የወጣችሁ አሸናፊ ተጫራቾች ይህ ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት አስር(10) ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ለም ሆቴል አካባቢ ኤም.ኤ.ህንጻ ላይ በሚገኘዉ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ 3ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 303 በመቅረብ የሚጠበቅባችሁን በማሟላት የሊዝ ውል እንድትፈጽሙ ጥሪያችንን እያስተላለፍን አንደኛ የወጡ ተጫራቾች ውል የማይፈጽሙ ከሆነ በሊዝ ደንቡ መሰረት አንደኛ የወጣው ተጫራች በሰጠው ዋጋ ዕድሉ 2ኛ ለወጡ ተጫራቾች የሚሰጥ በመሆኑና 2ኛ የወጡ ተጫራቾችም በተመሳሳይ ውል የማይፈጽሙ ከሆነ 3ኛ የወጡ ተጫራቾች አንደኛ የወጣው ተጫራች በሰጠው ዋጋ እንዲዋዋሉ በሊዝ ደንብ 162/2016 እና በተጫራቾች መመሪያ ላይ በተቀመጠዉ የጊዜ ሰሌዳ መሰረት በውስጥ ማስታወቂያ ጥሪ የምናደርግ መሆኑን እየገለጽን ለጨረታ ከወጡ 125 ቦታዎች ውስጥ የቦታ ኮድ LDR-LIMKMIX-00015231፣ LDR-KOL-MIX-00014974 እና LDR-KOL-MIX-00014975 ከጨረታ የተሰረዙ መሆኑን እናሳውቃለን፡