ህትመቶች

በ8ኛ ዙር የመሬት ሊዝ ጨረታ 2ኛ ለወጣቹ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር መሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ በንፋስ ስልክ ላፍቶ ፣ በኮልፌ ቀራንዮ ፣ በአቃቂ ቃሊቲ ፣ በየካ ፣ በአዲስ ከተማ፣ በቂርቆስ ፣ በጉለሌ እና በለሚ ኩራ ክ/ከተሞች የሚገኙና ለተለያዩ አገልግሎቶች የተዘጋጁ ቦታዎችን በጨረታ አወዳድሮ በሊዝ ለማስተላለፍ ታህሳስ 25 ቀን 2018 ዓ.ም በአዲስ ልሳን ጋዜጣ ማስታወቂያ በማውጣት ማጫረቱን ተከትሎ ከየካቲት 09 ቀን 2018ዓ.ም ጀምሮ ለአንደኛ አሸናፊዎች ጥሪ ተደርጎላቸዉ  የሊዝ ዉል መዋዋላቸው ይታወቃል፡፡
በመሆኑም የቦታ ኮዳቸው ከዚህ በታች የተገለጸ የሊዝ ቦታዎች አንደኛ የወጡ ተጫራቾች ውል ስላልፈጸሙባቸው በሊዝ ደንብ ቁጥር 162/2016 አንቀፅ 25 ንዑስ አንቀፅ 6 መሰረት ሁለተኛ የወጣችሁና ስማችሁ ከቦታ ኮዱ ጋር የተገለጸ ተጫራቾች አንደኛ አሸናፊ ያቀረበዉን ዋጋ እና ቅድመ ክፍያ በመክፈል መዋዋል የምትፈልጉ ከሆነ ከቀን 27/06/2018ዓ.ም ጀምሮ ባሉት 10/አስር/ ተከታታይ የስራ ቀናት በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሂሳብ ቁጥር 1000004337631 ቅድመ ክፍያዉን ገቢ በማድረግና የከፈላችሁበትን የባንክ ስሊፒ በመያዝ  በመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ ቀርባችሁ የሊዝ ዉል መዋዋል የምትችሉ መሆኑን እናሳዉቃለን፡፡ 
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር
መሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ