የህግና ቴክኒክ ጉዳዮች
የህግና ቴክኒክ ጉዳዮች ክትትል ቡድን መሪ ተግባርና ኃላፊነት
ተጠሪነቱ ለህግና ቴክኒክ ጉዳዮች ክትትል ዳይሬክተር ሆኖ የሚከተሉትን ተግባርና ኃላፊነቶች ያከናውናል፡-
- ከዳይሬክቶሬቱ ዕቅድ ጋር በተናበበ አግባብ የቡድኑን ዕቅድ ያዘጋጃል፣ በስሩ ለሚገኙ ባለሙያዎች ቆጥሮ ይሰጣል፣ ባለሙያዎች እንዲቅዱ ያደርጋል፣ አፈጻጸሙን በቅርበት ይከታተላል፣
 - በስሩ ያሉ ባለሙያዎች እንዲበቁ፣ እንዲበረታቱ፣ በጋራ የመስራት ባህል እንዲዳብር ያስተባብራል፣
 - የባለሙያ ክህሎትና አመለካከት ክፍተት የሚሞላ ሥልጠና እንዲሰጥ የስልጠና ፍላጎት ይለያል፣ ስልጠና እንዲሰጥ ጥያቄ ያቀርባል፣
 - ለቡድኑ የሚስፈልገውን የስራ መገልገያ ቁሳቁሶች ይለያል እንዲሟላ ጥያቄ ያቀርባል፣ ለባለሙያዎች ያሰራጫል፣ ስራ ላይ መዋሉን ይከታተላል፣
 - በክ/ከተሞች ለሚደረግ ድጋፍና ክትትል ዕቅድና ቼክ-ሊስት እንዲዘጋጅ፣ በተቀመጠው መርሃ-ግብር መሰረት ድጋፍና ክትትሉን ያስተባብራል፣ ሪፖርት አዘጋጅቶ ያቀርባል፣
 - ቢሮው በሚከሰስበት ወቅት ውጤታማ ክርክር ለማድረግ እንዲያስችል ተገቢው የሰነድ ማስረጃ እንዲጣራ እንደአስፈላጊነቱ የመስክ ልኬት እንዲከናወን የቡድኑን ባለሙያዎች ያስተባብራል፣ የተዘጋጀውን ማብራሪያ እና ማስረጃ በማደራጀት ያቀርባል፣
 - ቢሮው በተከሰሰባቸው ጉዳዮች የባለሙያ ምስክርነት አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ አግባብነት ያላቸው ባለሙያዎች ምስክር እንዲሰጡ ያስተባብራል፣
 - የፍትህ አካላት ለሚያቀርቧቸው የመረጃ እና ልዩ ልዩ የማብራሪያ ጥያቄዎች ተገቢውን ማስረጃ እንዲጣራ ባለሙያዎችን ያስተባብራል፣ የተዘጋጀውን የውሳኔ ሀሳብ በማረጋገጥ ያቀርባል፣
 - ከፖሊስ፣ ወንጀል ምርመራ እና ከወንጀል ጉዳዮች ጋር በተያያዘ ለሚቀርብ የባለሙያ ምስክርነት ጥያቄ አግባብነት ያላቸው ባለሙያዎች መረጃ እንዲሰጡ ያስተባብራል፣
 - የመፈጸም አቅምን ለማሳደግ እንዲያግዝ ለባለሙያዎችና አመራሮች በአዋጅ፣ ደንብ፣ መመሪያዎችና የአፈጻጸም ማኑዋሎች ላይ የስልጠና ፍላጎት ይለያል፣ የስልጠና ሰነድ በማዘጋጀት ያቀርባል፣
 - ስራ ላይ የዋሉ ደንቦች፣ መመሪያዎች፣ ማስፈጸሚያ ማኑዋሎች እና አሰራሮች ላይ የሚያጋጥሙ የአፈጻጸም ችግሮችንና ማሻሻያ የሚያስፈልጋቸውን ጉዳዮች ከሚመለከታቸው የስራ ክፍሎች ጋር በመሆን በጥናት ይለያል፣
 - በየስራ ክፍሎቹ የሚዘጋጁ የአፈጻጸም ማኑዋሉችን ላይ ከህግ አኳያ ድጋፍ እና ዕገዛ ያደርጋል፣ ያስተባብራል፣
 - ከአገልግሎት አሰጣጥ ጋር በተያያዘ ለሚቀርቡ የማብራሪያ ጥያቄዎች ተገቢውን የማጣራት ስራ እንዲከናወን ያደርጋል፣ የሚቀርበውን የውሳኔ ሀሳብ በማጋገጥ ያቀርባል፣
 - ቢሮው በሚሰራቸው ስራዎች ወይም በሚያደርጋቸው የግዥ ውሎች ጋር በተያያዘ የሚቀርብ የህግ አስተያያት ምክረ ሀሳብ እንዲዘጋጅ ያደርጋል፣
 - ቡድኑ ከሚያከናውናቸው ስራዎች ጋር በተያያዘ ለሚቀርብ ቅሬታ እንዲጣራ ያደርጋል፣ የተዘጋጀውን ምላሽ አረጋግጦ ያቀርባል፣
 - ዕለታዊ፣ ሳምንታዊ፣ ወርሃዊና የሩብ ዓመት የሥራ አፈጻጸሞችን በስሩ ከሚገኙ ባለሙያዎች ጋር ይገመግማል፣ ሪፖርትን ያቀርባል፣
 - በሚቀመጠው አሰራር መሰረት በስሩ የሚገኙ ባለሙያዎችን ይመዝናል፣ ለዳይሬክተሩ ያቀርባል፣
 - በዳይሬክተሩ የሚሠጡትን ሌሎች ተጨማሪ ሥራዎችን ያከናውናል፣