የመሬት ማህደር አስተዳደር
የይዞታ ማህደር አስተዳደር ድጋፍና ክትትል ቡድን መሪ ተግባርና ኃላፊነት
ተጠሪነቱ ለተቀናጀ መሬት መረጃና ማህደር አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ሆኖ የሚከተሉት ተግባርና ኃላፊነቶች ይኖሩታል፡-
- ከዳይሬክቶሬቱ ዕቅድ በመነሳት የቡድኑን እቅድ በወቅቱ አዘጋጅቶ ያቀርባል፣ ሲጸድቅም ስራዎችን ለባለሙያዎች በማከፋፈል ተግባራዊ አፈጻጸሙን ይከታተላል፤
 - በቡድኑ የሚገኙ ባለሙያዎችና ሰራተኞች የስራ ተነሳሽነታቸው እንዲጨምርና ውጤታማነታቸው እንዲጎለብት በቅርበት ይደግፋል፤
 - አስፈላጊ የሆኑ የስራ መገልገያ መሳሪያዎች እንዲሟሉ ያስደርጋል፤
 - እያንዳንዱ የቡድኑ አባል በተቀመጠው ስታንደርድ መሰረት ተግባራትን ማከናወናቸውን ይከታተላል፤ይደግፋል፣
 - ተገልጋዮች ለሚጠይቋቸው የማህደር ኮፒ ጥያቄዎች ምላሽ እንዲሰጥ ያደርጋል፣
 - አዳዲስ የአሠራር ስልቶችን በማጥናት ተግባር ላይ እንዲውሉ ያደርጋል፣
 - ለመብት ፈጠራ ስራ በቅርንጫፍ የተደራጁ መብት የሚፈጠርላቸውን ይዞታዎች ማህደራት ይረከባል ያደራጃል
 - ስካን የተደረጉ መብት ያልተፈጠረላቸው ይዞታዎች ማህደር ካለ በሶፍት ኮፒ ይረከባል፣
 - ለመብት ፈጠራ ስራ የተረከባቸውን ማህደራት በየክፍለ ከተማው ለይቶ አደራጅቶ ይይዛል ፣ ለአገልግሎት ዝግጁ ያደርጋል ያስተዳድራል፤
 - ለመብት ፈጠራ ቡድን ለአገልግሎት የሚፈለጉ ማህደራትን ሲጠየቅ ያስረክባል/ያቀርባል፤
 - በመመሪያው መሰረት ለመብት ፈጠራ ስራ ወጪ የተደረጉ ማህደራት መመለሳቸውን ይከታተላል፤
 - መብት ተፈጥሮላቸው የተጠናቀቁ ማህደራት በሚወጡ አሰራርና ፕሮግራሞች መሰረት ለክፍለ ከተማ ርክክብ እንዲደረግ ክትትል ያደርጋል፤
 - የማህደር መጥፋት ችግሮችን ይለያል በተቀመጠው አሰራር/መመሪያ መሰረት እንዲፈፀም ያደርጋል/ይፈፅማል/ ማህደራት ጠፍተው በማይገኙበት ሁኔታ ላይ ሲሆኑ ሙሉ ኃላፊነት በመውሰድ ተገቢውን እርምጃ ይወስዳል/ያስወስዳል
 - የመሬት ማህደራትን በሶፍት እና ሃርድ ኮፒ እንዲደራጁ ያደርጋል፤
 - ልዩ ልዩ መረጃ ኮፒ /ባክ አፕ መረጃ/ እንዲሰጥ ይፈቅዳል
 - የመሬት ማህደራት በአግባቡ መያዛቸውን፣ በዘመናዊ መንገድ መደራጀታቸውን ይከታተላል
 - በክፍሉ የሚገኙ ማህደራትን እያንዳንዱ ገጽ ቁጥር እንዲሰጠውና አባሪ ተመትቶ እንዲቆጠር ያደርጋል
 - የሚመራቸው ሰራተኞች ልምድ ካላቸው አቻ ተቋማት ተሞክሮ እንዲወስዱ ያደርጋል
 - ለሚያጋጥሙ ችግሮች ግብረ-መልስ ይሰጣል
 - የክትትልና ድጋፍ እቅድና ቼክ-ሊስት ያዘጋጃል
 - የመሬት ማህደራትን ኮፒና ስካን በማድረግ ለመሬት ይዞታ ምዝገባና መረጃ ኤጀንሲ እንዲተላለፉ ሥራውን በጥብቅ ዲሲፕሊን ይመራል፤ይቆጣጠራል፤
 - የይዞታ ማረጋገጥ ስራው ሲጠናቀቅ ዋናዉ የይዞታ ማህደራት ለመሬት ይዞታ ምዝገባና መረጃ ኤጀንሲ መተላለፉን ያረጋግጣል፤
 - ያጋጠሙ ችግሮችን ይለያል፤ መፍትሄ ይሰጣል፤
 - ቡድኑ ለተገልጋዮች የሚሰጣቸው አገልግሎቶች በአግባቡ መሰጠታቸውን እና ቅሬታም እንዳይከሰት ይከታተላል፤ቅሬታም ሲፈጠር ማስተካከያ ይሰጣል፣
 - ከላይ የተዘረዘሩትን ተግባራት በተቀመጠላቸው የጊዜ ሰሌዳ መሠረት የአፈፃፀም ሪፖርት በማዘጋጀት ለሚመለከታቸው ክፍሎች ያሳውቃል፣
 - ሌሎች ከሥራ ክፍሉ ጋር ተዛማጅ የሆኑ ስራዎችን በበላይ ኃላፊ ሲመራለት ያከናውናል
 - የስራ አፈጻጸም ይመዝናል፤ይገመግማል፤ክፍተቶችን ይለያል፤የተለያዩ የአቅም ማጎልበቻ አማራጮችንም በመለየት ተግባራዊ ያደርጋል፤