የመሬት ዝግጅት ባንክና ጥበቃ
 የመሬት ዝግጅት ባንክና ጥበቃ ቡድን መሪ ተግባርና ኃላፊነት
ተጠሪነቱ ለመሬት ዝግጅት ባንክና ጥበቃ ዳይሬክቶሬት ሆኖ የሚከተሉትን ተግባርና ኃላፊነቶች ያከናውናል፡-
- ከክፍሉ ስትራቴጂ እና ዓመታዊ እቅድ በመነሳት የቡድኑን እቅድ እና ራስን የማብቃት ዕቅድ ያዘጋጃል፤
 - ከስሩ ከሚገኙ ባለሙያዎች ጋር በዕቅዱ ዙሪያ ውይይት በማካሄድ የጋራ ግንዛቤ እንዲፈጠር ያደርጋል፣ የቡድኑን ዕቅድ የመጨረሻ ቅርጽ አስይዞ ለበላይ ሀላፊዎች ያቀርባል፣ያስተቻል፣ያጸድቃል፣ እንዲተገበር ያደርጋል፡፡
 - ለሥራ ክፍሉ አስፈላጊ የሆኑ ግብዓቶችን (የሰው ኃይል፣ በጀት፣ ቁሳቁስ) እንዲሟላ መረጃውን አደራጅቶ ለዳይረክቶሬቱ ያቀርባል፣በአግባቡ መሟላቱን ይከታተላል፣ያርጋግጣል፡፡
 - በስሩ ያሉ ባለሙያዎች የሥራ ዕቅድ ማዘጋጀቸውን፤ይከታተላል፣ይደግፋል፣ ያረጋግጣል፡፡
 - ባለሙያዎች ያቀረቡትን የስራ ዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ይመረምራል፣ይተቻል፣ ሪፖርቱ እንዲዳብር ድጋፍ ያደርጋል፣በየወቅቱ ይገመግማል፣ግብረ-መልስ ይሰጣል፡፡ ሪፖርቱን ለቅርብ ኃላፊው ያቀርባል፡፡
 - አገልግሎቱን ለመስጠት እንዲቻል ለባለሙያዎች ምቹ የሥራ ሁኔታና የመሥሪያ ቁሳቁሶችን ያመቻቻል፣
 - የቡድኑን ባለሙያዎች የአቅም ክፍተት በመለየት አቅማቸው የሚገነባበትን ሁኔታ ያመቻቻል፣
 - በአመት ሁለት ጊዜ የቡድኑን ባለሙያዎች የስራ አፈጻጸም በመመዘን ውጤት ይሰጣል፣ የተሻለ አፈፃፀም ያላቸው ባለሙያዎች ማበረታቻ እንዲሰጥ ያስተላልፋል ፡፡
 - የክፍት ወይም ባዶ ቦታዎችን መረጃ ለመሰብሰብ የሚያስችል መርኃ ግብር በማዘጋጀት በሚመለከተው አካል ያስጸድቃል ፡፡
 - የክፍት ቦታዎችን መረጃ ከጂ.አይ.ኤስ. (GIS) እና ከመስመር ካርታ (Line Map) ላይ ለመልቀም የሚያስችል የካርታ ማውጫ (Index Map) ያዘጋጃል/ እንዲዘጋጅ ያደርጋል፡፡
 - ክፍት የሆኑ ቦታዎችን በጂ.አይ.ኤስ. ካርታ፣ከመስመር ካርታና ከቤዝ-ማፕ እንዲለይ ያደርጋል፡፡
 - ክፍት የሆኑ ቦታዎችን ስኬች ይሰራል/ ያሰራል፤ባንክ መመዝገቡን ያረጋግጣል፡፡
 - በባንክ የተመዘገበን መሬት በቤዝ ማፕ ያወራርሳል፤ወጭና ቀሪውን ያቀናንሳል/እንዲቀናነስ መረጃውንም ያደራጀል፡፡
 - ለመሬት ዝግጅት ሽንሻኖ እንዲሰራ ይልካል፡፡
 - ለመሬት ዝግጅት ቡድን እንዲዘጋጅ ከተላከው ውስጥ ለልማት ያልተሸነሸነ ቀሪ መሬት በመረከብ፣ እንዲመዘገብ ያደርጋል፡፡
 - ተገቢ ባልሆነ አግባብ ይዞታዬ መሬት ባንክ ገባብኝ ለሚሉ አቤቱታዎች አጣርቶ ተገቢውን ምላሽ ይሰጣል፡፡
 - ክፍት የሆኑና ከማንኛውም አይነት የይገባኛል ጥያቄ ነጻ መሆናቸው የተረጋገጡ ቦታዎች መረጃ አደራጅቶ እንዲጠበቁ ያደርጋል፡፡
 - ጥበቃ እየተደረገላቸው የሚገኙ ቦታዎች በህጋዊ መንገድ ለልማት ሲተላለፉ አስፈላጊው ክትትል ተደርጎ የመረጃ ቋቱ ወቅታዊ ስለመደረጉና በመሰረታዊ ካርታ ላይ ስለመወራረሱ ክትትል ያደርጋል፡፡
 - የመሬት ጥበቃ ሂደትን ለመከታተል የሚያስችል የሱፐርቪዥን እቅድ ያዘጋጃል፤ በሱፐርቪዥን ማከናወኛ ቼክ ሊስት መሰረት ሂደቱን ሱፐርቫይዝ ያደርጋል፤መረጃ አደራጅቶ ግብረ-መልስ ይሰጣል፡፡
 - የመሬት ጥበቃ ስራ ላይ የሚታዩ የአፈጻጸም ክፍተቶችን ይገመግማል፣ ክፍተቶች ይለያል፣ ችግሮች ሲያጋጥሙ እንዲፈቱ ለሚመለከተው አካል ያሳውቃል፡፡
 - የህገ-ወጥ መሬት ወረራ ጥቆማ ትክክለኛ ሆኖ ሲገኝ ከሚመለከተው ባለድርሻ አካል ጋር በመተባበር ቦታው ለመንግስት ተመላሽ እየተደረገ ስለመሆኑ ይከታተላል፣መረጃው አደራጅቶ ለዘርፍ አሰተባባሪው ያቀርባል፡፡
 - የክትትል እና ድጋፍ ድርጊት መርሃ-ግብርና ቼክሊስት እንዲዘጋጅ ያደርጋል፣ ያስፀድቃል፡፡
 - በተዘጋጀው መርሀ ግብርና ቼክሊስት መሰረት የድጋፍና ክትትል ሥራ ያከናውናል፡፡
 - በድጋፍና ክትትል ስራ የተገኘው ግኝት መረጃ ያደራጃል ፤ግብረ መልስ ይሰጣል፡፡