የመልሶ ማልማት ትግበራ ክትትል ቡድን
	- የዳይሬክቶሬቱን እቅድ መሰረት በማድረግ የቡድኑን ዕቅድ ያዘጋጃል፤
 
	- በፀደቀው ዕቅድ መሰረት በቡድኑ ስር ለሚገኙ ባለሙያዎች ሥራ ቆጥሮ ይሰጣል፣ ያስተባብራል፣ ድጋፍ ይሰጣል፡፡
 
	- አገልግሎቱን ለመስጠት እንዲቻል ለባለሙያዎች ምቹ የሥራ ሁኔታና የመሥሪያ ቁሳቁሶችን ያሟላል፤
 
	- በቡድኑ ስር የሚገኙትን ባለሞያዎቸ የስራ አፈፃጸማቸውን በመከታተል፣ በመገምገም ተገቢውን  ግብረ መልስ ይሰጣል፤
 
	- በአፈፃጸም ላይ የሚያጋጥሙ ችግሮችን በመለየት መፍትሄ ይሰጣል፣ በሥራ ክፍሉ መወሰን የማይቻሉ ጉዳዮችና ቅሬታዎች ሲኖሩ ለዳይሬክተሩ በማቅረብ ያስወስናል፤
 
	- የፀደቀውን የከተማ ንድፍ ጥናት ሰነድ የትግበራ ክትትል ማከናወኛ ዝክረ ተግባርና ቼክሊስት እንዲዘጋጅ ያደርጋል፣ ለዳይሬከተሩ አቅርቦ ያስፀድቃል፤
 
	- በፕሮጀክቱ እቅድ መሰረት ትግበራውን የሚመመራ እና ክትትል የሚያደርግ ባለሙያዎችን እና ግብዓት ያሟላል፤
 
	- በየፕሮጀክቶቹ በዕቅዱ መሰረት ከህብረተሰቡና ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት መካሄዱን ይከታተላል፣ ቃለ-ጉባኤ መያዙን ያረጋግጣል፤
 
	- የአተገባበር መከታተያ መረጃ ማሰባሰቢያ መሳርያዎች /መጠይቅ፣ ቼክሊስት፣ ወዘተ/ መዘጋጀታቸውን ያረጋግጣል፤
 
	- የመረጃ መሰብሰብ ሂደቱ በትክክል መከናወኑ ይከታተላል፤
 
	- በመመሪያ 79/2014 መሰረት ካሳ እና ምትክ አገልግሎት የሚያስፈልጉ የልማት ተነሺ መረጃዎች በክፍለ ከተማ የልማት ተነሺዎች መረጃ አሰበሰብ ቡድን አማካይነት እንዲሰበሰብ ያደርገል፤
 
	- ልማት በሚከናወንበት ቦታ ያሉ ነዋሪዎች ከተነሺዎች መልሶ ማቋቋም ጋር በመሆን አስፈላጊውን መስተንግዶ ማግኘታቸው እና ተነሺዎች ለመነሳት ዝግጁ መሆናቸውን በመከታተል እንዲረጋገጥ ያደርጋል፡፡
 
	- በጥናቱ መርሃ-ግብር መሰረት ቦታ ማጽዳት ስራ መካሄዱንና መሰረተ ልማት መሟላቱን ክትትል ስራው እንዲከናወን ያደርጋል፤
 
	- ጥናቱ በሚተገበርበት ወቅት የሚያጋጥሙ የጥናት እና የመረጃ አሰባሰብ ክፍተቶችን በመለየት በወቅቱ የእርምት እርምጃ ይወስዳል እንዲሁም ለቀጣይ ጥናት መነሻ ግብዓት እንዲሆን ያመቻቻል፤
 
	- ፕሮጀክቶቹ ወይም የልማት ስራዎቹ በተያዘላቸው ዕቅድ መሰረት በአግባቡ እየተተገበሩ መሆናቸውንና አጠቃላይ አፈጻጸሙን በመከታተል ሪፖርት ያደርጋል፤
 
	- ከመልሶ ማልማት ቦታ የሚነሱ ባለይዞታዎች በግል ይዞታቸው በልማት አከባቢ በተዘጋጀው የከተማ ንድፍ ጥናት መሰረት ሊያስገነባ የሚያስችል ቦታ ስፋትና የማልማት አቅም (መመሪያ ቁጥር 79/ 2014)  በተፈቀደ ጊዜ ገደብ  ማልማት የሚችለትን በመለየት ይመዘግባል መረጀ አደራጅቶ ለዳይሬክቶሬቱ ያቀርባል 
 
	- በኩታ ገጠም ይዞታቸወን በመቀላቀል በጋራ የአከባቢው ዲዛይን ሊያስገነባ የሚችል ቦታ ስፋት እና የማልማት አቅም (በመመሪያ ቁጥር 79/ 2014) በተወሰነ ጊዜ ለማጠናቀቅ ውል ገብተው  ቅድሚያ ማልማት የሚፈልጉትን አደራጅቶ ለዳይሬክቶሬቱ ያቀርባል፤
 
	- በካሳና ምትክ መስተንግዶ መመሪያ ቁጥር 79/ 2014 የሚሰጠውቸው ምትክ ይዞታ ስፋት መጠን በጋራ ተደራጅቶ ለአከባቢ ከተማ ንድፍ ሊያስገነባ የሚያስችል የቦታ ስፋት ለማልማት የሚፈልጉትን ከወሰን ማስከበር ዳይሬክቶሬት ጋር በጋራ በመሆን ይመዘግባል መረጃ አደራጅቶ ከውሳኔ ሀሳብ ጋር ያቀርባል፣
 
	- በካሳና ምትክ መስተንግዶ መመሪያ ቁጥር 79/ 2014 መሰረት ተሰልቶ የሚሰጠው ገንዘብ ልክ በልማት አካባቢ ከሚገነበው የመንግስት ቤት ምትክ እንዲሰጥ ለውሳኔ ያቀርባል፤
 
	- በልማቱ ምክንያት ተነሺ የሆኑ እና ምንም ገቢ የሌላቸው ተነሺዎችን መልሶ የማቋቋሚበት እና የስራ ዕድል የሚያገኙበትን ሁኔታ ከተነሺዎች መልሶ ማቋቋም ጋር በጋራ ያመቻቻል፤
 
	- ለማዕከላትና ለኮሪደሮች ልማት ከተዘጋጁ ቦታዎች በዝርዝር ዲዛይን መሰረት በመንግስትና በግሉ ዘርፍ የሚለሙ ቦታዎችን በፕላን ፎርማት በማዘጋጀት ለዳይሬክቶሬቱ ያቀርባል፤
 
	- በቢሮ ፕሮሰስ ካውንስል ውይይት ከተደረገ በኃላ በከተማው ካቢኔ ሲጸድቅ ተግባራዊ እንዲደረግ ሲመጣ በውሳኔ መሰረት ስለመፈፀሙ ክትትል ያደርጋል፤
 
	- ለማዕከላትና ለኮሪደሮች ልማት ከተዘጋጁ ቦታዎች ውስጥ በግሉ ዘርፍ እንዲለማ የተለየ ቦታ በመስክ ሰርቨይ ተደርጎ ሽንሻኖ ተሰርቶ እንዲዘጋጅ ያደርጋል፣
 
	- የከተማ መዋቅራዊ ፕላን እና ዝርዝር የአካባቢ ልማት ፕላኖች መሰረት በማድረግና ፍትሃዊና ኢኮኖሚያዊ የመሬት ልማትና አቅርቦት እንዲኖር ይሰራል፤
 
	- አከባቢ ልማት ፕላንና በጸደቀላቸው የማዕከላትና ኮሪደሮች ቦታዎች ላይ በዕቅድና በዝርዝር ዲዛይን ያልተደገፈ ግንባታ እንዳይኖር ወይም እንዳይካሄድ ከሚመለከተው አካል ጋር በኃላፊነት ይከታተላል፣ ይቆጣጠራል፤
 
	- በከተማው ካቢኔ ውሳኔ መሰረት የመሰረተ ልማት ዘርጊ ተቋማት በተቀናጀና በጋራ በሚዘጋጀው ዕቅድ መሰረት ወደ ግንባታ እንዲገቡ የተፈረመው ስምምነት ተፈጸሚነቱን ክትትል ያደረጋል፤
 
	- በማእከላትና ኮሪደሮች ልማት አከባቢ የሚካሄዱ ልማቶች በተቀመጠላቸው ከተማ ንድፍና ፣ ቅደም ተከተልና ጊዜ ገደብ እንዲለሙ ድጋፍ ያደርጋል፣ አፈጻጸሙን ይከታተላል፤
 
	- በማእከላትና ኮሪደሮች ልማት አከባቢ የሚካሄዱ ልማቶች በውል መሰረት ከልተፈጸመ በውሉ እና በሊዝ ህግ መሰረት ህጋዊ እርምጃ እንዲወሰድ መረጃ አደራጅቶ ከውሳኔ ሀሳብ ጋር ያቀርባል አፈጻጸሙን ይከታተላል፤
 
	- የማእከላትና ኮሪደር አከባቢ ልማት የዓለም አቀፍ  እና አገር ተሞክሮዎችን ይወስዳል ፣ ያደራጀል በከተማው ነበራዊ ሁኔታ የሚፈጽመበት ስልት ይቀይሳል፤
 
	- የአፈፃፀም ሪፖርት በየጊዜው አዘጋጅቶ ያቀርባል፤